በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር ክልላዊ ዝግጅቶች በየደረጃው መጀመራቸውን ቢሮአስታወቀ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር ክልላዊ ዝግጅቶች በየደረጃው መጀመራቸውን ቢሮአስታወቀ፡፡

አቶ አማረ ዓለሙ

የክልሉ ሥራና ስልጠና ቢሮ እንዳስታወቀው በተያዘው በጀት ዓመት ለ4ኛ ጊዜ ‹‹ ብሩህ አዕምሮዎች ፣በክህሎት የበቁ ዜጎች!››በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቆ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል።በዚህም በአሰልጣኞችና ሰልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች ክልሉን የሚወክሉተወዳዳሪዎችን ለመለየት በየደረጃው በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውድድር መካሄድ መጀመሩን የቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

አቶ አማረ ዓለሙ ገልፀዋል፡፡

ለአብነት በባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውድድሩ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አማረ በተቋማ ደረጃ የሚካሄደው ውድድር እንደተጠናቀቀ በክላስተርና በክልል ደረጃ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክልል ደረጃ ከመጋቢት መጨረሻ እስከ ሚያዚያ መጀመሪያ 2017 ዓ/ም በኮምቦልቻ ከተማ የሚከተሉት ውድድሮች እና ሁነቶች ይከናወናሉ ብለዋል :-

1/ በ2015 ዓ/ም እና በ2016 ዓ/ም ከአነስተኛ መብቃት ወደ ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ ሽግግር ያደረጉ 420 ኢንተርፕራይዞችን እውቅና መስጠትና ለክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ርክክብ መፈፀም

2/ በአሰልጣኞች፤ሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞች 75 ቴክኖሎጅዎች ቀርበው ይወዳደራሉ ለአሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል፤

3/ በ22 ሙያዎች በ110 ሰልጣኞች መካከል የክህሎት ውድድር በማካሄድና ለአሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል፤

4/ በአሰልጣኞች 10 የተግባር ጥናትና ምርምር ጽሁፎች ቀርበው ውድድር ይካሄድባቸዋል ለአሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል፤

5/ በወጣቶች 34 ሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ቀርበው ውድድር ይካሄድባቸዋል እውቅናና ሽልማት ይሰጣል፤

6/ 80 ኢንተርፕራይዞች በንግድ ትርኢት፤ኤግዚብሽንናባዛር ምርታቸውንና አገልግሎታቸውን አቅርበው ያስተዋውቃሉ፤

የገበያ ትስስር ይፈጥራሉ፤

7/ በክልሉ በፌደራል ደረጃ የሚካሄደው በክህሎት በቴክኖሎጅ ፤ በተግባር ምርምር ስራዎች እና በወጣቶች

ሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ ለአሸናፊነትና ለውጤት ይወዳደራሉ፤

በመጨረሻም ም/ሃላፊው አቶ አማረ አለሙ ውድድሩ

እና ሁነቱን የአካባቢው ማህበረሰብ በአካል በመገኘት እንዲመለከት እና የጥ/አ/ኢንተርፕራይዝ ምርቶች እንዲሸምቱ ጥሪ አስተላዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *