የስራ ዕድል መፍጠሪያ ፀጋዎችን ለይቶ ተግባራትን በቅንጅት በመፈፀም ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል።

የስራ ዕድል መፍጠሪያ ፀጋዎችን ለይቶ ተግባራትን በቅንጅት በመፈፀም ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል።

******************

የካቲት 29/2017ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ የ2017በጀት ዓመት የ8ወር የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ የውይይት መድረክ ከመምሪያ እስከ ክፍለ ከተማ ያሉ ፈፃሚዎችና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሄደ።

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስምንት ወራት ለ20,482 ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በ 8 ወሩበቋሚና ጊዚያዊ ለ9,430 ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር የእቅዱን 46% መፈፀም መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ መኮንን ሙላዳም ገልፀዋል።

የቀሩን ጥቂት ወራት በመሆናቸው እቅዱን ለማሳካት ፀጋዎችን ለይተን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በውጭ አገር የስራ ስምሪት ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ ሰፊ የግንዛቤ ስራ የሚጠይቅ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

የስራ እድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶች የገበያ ትስስር መፍጠር ይኖርብናል ያሉት መምሪያ ሃላፊው በኢንተርፕራይዝና በግል የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገሩ ቁጠባን እንዲለምዱ መስራት ከተቋማችን የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ በልዩ ትኩረት መስራት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።

ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠሪያ በተዘዋዋሪ ብድር ተሰራጭቶ ያልተመለሰውን ገንዘብ ጨምሮ ዚያቸው ያለፈባቸው ኮንቴነርና ሸዶችን በማስመለስ ለሌሎች ወጣቶች ለማስተላለፍ ቀጣይ በርብርብ የምንሰራው ተግባር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ሃላፊው ወጣቶችን ለማብቃት በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ስራችን ክፍተት ያለበት ስለሆነ ይህን ለማስተካከል በንቅናቄ መስራት ይኖርብናል ሲሉ አቶ መኮንን አሳስበዋል።

የወጣቱ የስራ ዕድል ፈጠራን ሁሉም የራሱ ተግባር አድርጎ ሊያግዝ ይገባል ያሉት አስተያይታቸውን የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እየሰራን ነው፤ቀጣይ ይህን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የስራ ዕድል ፈጠራ ነው፤ ይህ ዘርፍ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ቁልፍ ተግባር ነው ያሉት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን በከተማችን የስራ ዕድል በአብዛቸው በአገልግሎት ዘርፉ ነው እየተፈጠረ የሚገኘው፤ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፎችም ሰፊ ዕድል ስላለ በትኩረት መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

ፀጋን ለይቶ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ላይ ያሉ ክፍተቶች መታረም ይኖርባቸዋል ያሉት ምክትል ከንቲባው የቆይታ ጊዜ ያለፈበቻው ሸዶችና ኮንቴነሮች የመረጃ ችግርና ቁርጠኝነት እንዲሁም የቅንጅት መጓደል ይስተዋላል፤ ይህን ቀጣይ ተቋሙ ማስተካከል ይኖርበታል ብለዋል።

ተቋሙ በቅርቡ ምሩቃን ወጣቶችን አግኝቶ ውይይት ማካሄዱ የሚመሰገን ተግባር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ስለሽ ወጣቶች ያነሷቸውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የመረጃ አያያዝን ማዘመን፣ተግባራትን አቀናጅቶ መፈፀምና

በቀሪ ጊዚያት የነበሩ ስኬቶችን በማጠናከርና ክፍተቶችን በማረም ለተሻለ ውጤት መስራት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

SEED ፕሮጀክት በተዘዋዋሪ ብድር ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና ያለውን ክፍተት ለማገዝ ለከተማችን ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ስለሆነ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን መለዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዕለቱም ቀጣይነት ባለው የስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞችን ማሳደግ /SEED/ፕሮጀክት ስለሚሰራቸው ተግባራት በፕሮጀክቱ ሰራተኞች ገለፃ የደረገ ሲሆን በ10% ወለድ ከ 60ሺ 150ሺ ብር ብድር የማመቻቸትና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ቴሌግራም https://t.me/debremarkoscommunication

ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *